Debre Mihret St michael EOTC
ሼፊልድ ደ.ም ቅዱስ ሚካኤል ኢኦተቤክ
EN አማ

ሼፊልድ ቅዱስ ሚካኤል ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

እንኳን ወደ አገልግሎታችን መጡ

ተጨማሪ ያንብቡ

የደብሩ አስተዳዳሪ
ቀሲስ ወንድዎሰን መልእክት

የቀደሙ አባቶቻችን ብዙ ስራ ሰርተው የብርሃን ችቦውን አብርተው በክብር አስረክበውን አለፉ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመልሶ በማስተማር በዓለም የመጀመሪያው ተብሎ በታሪክ ጸሐፊው በአውሳብዮስ የተመሰከረለት (ሥራ ም. 8) ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ብርሃነ ወንጌልን በመቅረዘ ኦሪታችን ላይ ለኮሰው በዚህም ቤተክርስቲያናችን በሐዋርያት ትምህርት አምና ጥምቀትን ኢየሩሳሌም ተጠምቃ በራሷ ሐዋርያ ትምህረተ ወንጌልን በማግኘት የመጀመርያዋ አድርጏት ለሌሎች ወንድሞቹ አስረከበ ከሣቴብርሃን አባ ሰላማ ዘጠና ዘጠኙ ቅዱሳን ቅዱስ ያሬድ ስልጣኑን አስረክቦ ዘውዱን ኢየሩሳሌም ልኮ ገዳም የገባው ጻድቅ ንጉሣችን ዐፄ ካሌብ እና ሌሎቹም አባቶች ታላላቅ ስራ ሰርተው ለልጆቻቸው አስረከቡ ቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ክርስትና ሃይማኖትን ህይወትን ከምግባር ዶግማውን ከቀኖና

አስራውን ከአዋልድ ታሪክን ከትውፊት ስራን ከቅርስ ዛሬም ድረስ ህያው ምስክር ሆነው የምናያቸውን ውብ ስርዓተ አምልኮ ለኛ ለልጆቻቸው አድርሰውልናል እንደሚታወቀው ክርስትና የምንኖረው ህይወት በመሆኑ ከአባቶቻችንም እንደተማርነው በደረስንበት በተሰደድንበት ቦታ ሁሉ በስሙ መሰብሰብ (ማህበር)ቅዱሳንን መዘከር አልፎም የቃልኪዳኑም ታቦት አብሮን ተሰዶ ቤተክርስቲያን መመስረት ይህ ሐዋርያዊ ሰንሰለትነት ያለው የሚገባም ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት ደብራችን ተመስርቶ እዚህ ደርሷል እኔም እድል ገጥሞኝ የዚህ ደብር አገልጋይ ከሆንኩበት ጊዜ አንስቶ የነበረውን ይህንኑ የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተል ከካህናት አባቶቼ ወንድሞቼ ዲያቆናት እንዲሁም ከማህበረ ምዕመናኑ ጋር በመሆን አገልግሉቶን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስረከብ በእግዚአብሔር ቸርነት በሊቀመላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት እያገለገልን እንገኛለን

አገልግሎቶቻችን

የክርስትና ጥምቀት አገልግሎት

ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ከፊል ስሙ ነው። ይህንን ስም የሚያገኘው እና የእግዚአብሔር ልጅ የሚባለው በጥምቀት ነው። ዮሐ3፥5 ሮሜ 8፥18 ወንድ ከሆነ በ40 ቀኑ ሴት ከሆነች ደግሞ በ80 ቀናቸው ይፈጸምላቸዋል።

የቅዳሴ አገልግሎት

ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

ጋብቻ

የክርስቲያኖች ጋብቻ በቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸም ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም የሚያሰጥ ስለሆነ ከሰባቱ ምሥጢራት እንዱ ነው ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለው ።

ጸሎተ ፍታት

ለሙታን የሚደረግ ጸሎት የቤተክርስቲያንን አንድነት ከማመን የሚመጣ ነው ቤተክርስቲያን በሁለት ወገን የሚኖሩ ልጆች አሏት በአፀደ ስጋ በምድር እና በአፀደ ሥጋ በሰማይ ሁለቱም የአንዲት ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው

የሠንበት ትምህርት

ዘወትር ቅዳሜ ከ 15:00-17:00 ሰአት በቤተክርስቲይን አዳራሽ Upper Hanover Street S3 7RQ የነገ ቤተክርስቲያንን ተረካቢ ብሎም ሀገርን የሚመራ ትውልድ ለማፍራት፣ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው ትውልድ ለማፍራት መማር ያስፈልጋል።

የእሁድ ጉባኤ

የቅዳሴ እገልግሎት በማይኖርብት ሳምንት እህድ ከሰዓት በኃላ 13:00-15:00 ይኖረናል :: በዋትሳፕ ግሩፕና በዚሁ ድህረ ገፅ ወቅታዊ አገልግሎቶችን ይከታተሉ ዘንድ እንጠይቃለን::

ቤተክርስቲያኑን ይደግፉ

ቤተክርስቲያኑን ለማሳደግ እና ለማገልገል ይረዱን። የምትሰጡት የገንዘብ ድጋፍ የአብያተ ክርስቲያኑን ሕይወት ይደግፋል።

አሁን ይለግሱ